
Category 1
የስልጠናው ዋና ዋና አላማዎች
- ሰልጣኞች የስራ ፈጠራ እና ስራ ፈጣሪ ምንነት በመገንዘብ ጠንካራ የስራ ባህል
በመፍጠር የህብረተሰቡን ተጠቃሚነት እንዲያረጋግጡ ማድረግ ነው፡
- በግል ስራ ላይ መሰማራት ለአንድ ሰው በኢኮኖሚ እራስን ለመቻል
እና ለማደግ ዋና አማራጭ እንደሆነ ማወቅ
- የውጤታማ የስራ ፈጣሪ ብቃቶችን በደንብ ማወቅና ማብራራት መቻል
- ስራ ፈጣሪ ለመሆን የሚያስችሉ አማራጮችን በመለየትና
በማወቅ አዋጭ የንግድ ሃሳብ ማመንጨት እና የንግድ ድርጅት ባለቤትነት መሆን
- የንግድ ስራ እቅድ እንዴት እንደሚዘጋጅ እና መሰረታዊ
ይዘቶች ምን ምን እንደሆኑ በማወቅ ጠንካራ የንግድ ስራ እቅድ ማዘጋጀት
- የሂሳብ መዝገብን ዓላማ እና ጥቅሞችን እና የአመዘጋገብ ሂደቶችን
በመረዳት የሂሳብ መዝገብ መዝግቦ መያዝ መቻል